Ethiopian Medical Equipment Digital Marketplace

Ethiopian Medical Equipment Digital Marketplace

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ለ2017 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ አገልግሎቶችና እቃዎች በአገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Image
img
Free
Ref No
Company Info
Published On
Region
Tender Category
Contact Phone
Contact Email
Remaining Date
Bid Open Date
Bid Close Date
Publish Date
Bid Bond
Bid Type
Tender Doc Price

የጨረታ ማስታወቂያ
የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ እና አበበች ጎበና እናቶችና ህጻናት ሆስፒታል
ጨረታ ቁጥር 04/2017 ዓ.ም የተጫራቾች መመሪያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ለ2017 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አገልግሎቶችና እቃዎች በአገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት ፡-1 የኔት ወርክ እቃዎች ግዥ
  • ሎት ፡-2 የሲስተም ማስተካከያ ስራዎች /support, maintenance, development optimization of student information system/
  • ሎት ፡- 3 የህክምና መገልገያ መሳሪያ እቃዎች
  • ሎት ፡-4 የህክምና መድኃኒት እና ሰፕላይ ግዥ

በዚሁ መሰረት በዘርፉ የተሰማራችሁ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹትን በማሟላት መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

  1. ተወዳዳሪዎች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/፣ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ማረጋገጫ የጨረታ መሳተፊያ የገቢዎች /ክሪላንስ/፣ የፌድራል ግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢነት ምዝገባ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ሰርተፍኬት የማይመለስ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
  2. የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ሆስፒታሉ ድረስ ቀርባችሁ ለሎት 1 እና 2 ለእያንዳንዱ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ እንዲሁም ለሎት 3 እና 4 ለእያንዳንዱ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ከግዥ ዳይሬክተር ቢሮ መውሰድ ትችላላችሁ።
  3. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም ጨረታው ለ10 የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከ2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይቻላል።
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ የሰነድ ኮፒ ኦርጅናል እና የዋጋ ማወዳደሪያ ኦርጅናል ለየብቻ እና የሰነድ ኮፒ እና የፋይናሽያል ኮፒ ለየብቻ በድምሩ በ4 ፖስታ በማሸግ ማህተም በመምታት የሚወዳደሩበትን ሎት በመጻፍ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ፣ ደረሰኝ በኦርጅናል ቴክኒካል ፖስታ ውስጥ አብሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን ገንዘብ ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1 እና 2 ለእያንዳንዱ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር እንዲሁም ለሎት 3 እና 4 ለእያንዳንዱ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ተብሎ በተዘጋጀ የባንክ የተመሰረተለት ሲፒኦ ወይም ጋራንት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6.  ለእቃ ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ሆስፒታሉ ድረስ ያቀርባል።
  7.  ለአገልግሎት ግዥ ተቋሙ በሚያወጣው ቴክኒካል መስፈርት መሰረት የሚመዘን መሆኑን እናሳውቃለን።
  8. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ከቫት ጋር መሆን አለበት ይህ ካልሆነ ግን ግዥ ፈጻሚው የተሞላው ዋጋ ከነቫቱ እንደሆነ በመቁጠር ያወዳድራል።
  9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ብቻ በግልጽ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላት በግርጌው ስም፣ ፊርማ እና የድርጅታቸውን ማህተም በማኖር አሸጎ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ግዥ ዳይሬከተር ቢሮ ውስጥ በማስገባት መወዳደር የምትችሉ ሲሆን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመቁጠር በ11ኛው የስራ ቀን (ቅዳሜ እሁድ ከሆነ ለሰኞ በማድረግ) 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እናሳውቃለን።

ለበለጠ መረጃ ስልክ 0963002419
አድራሻ፡- የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በየካቲት 12 ሰማዕታት ሐውልት ፊት ለፊት
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የአዲስ አበባ አስተዳደር ጤና ቢሮ የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ

No clarification Available

# Lot Price Lot Number Action

Sign up as .....